General
የፒኤስጂ እና ባርሴሎናን ጨዋታ ማን ይመራል ?
TIKVAH-SPORT · 20 Oct 2026, 00:19
ፒኤስጂ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
ጨዋታውን እንግሊዛዊው ዳኛ ማይክል ኦሊቨር በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
ማይክል ኦሊቨር ስድስተኛ የባርሴሎና ጨዋታቸውን የሚመሩ ይሆናል።
ባርሴሎና በማይክል ኦሊቨር እየተመራ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አንዱን ነው ማሸነፍ የቻለው።
ባርሴሎና በሁለቱ ጨዋታዎች ተሸንፎ ፤ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል።
የፒኤስጂ እና ባርሴሎና ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት 4:00 ሰዓት ፓርክ ዴ ፕሪንስ ስታዲየም ላይ ይደረጋል።
